የኢትዮጵያ ሚድዋይፎች ማህበር የውሃ ማጣሪያዎችን ለጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል በስጦታ አበረከተ

የኢትዮጵያ ሚድዋይፎች ማህበር ግምታቸው 45000 ብር የሆኑ አምስት የውሃ ማጣሪያዎችን ለጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል በስጦታ አበርክቷል፡፡  የውሃ ማጣወሪያዎቹ ውሃን ከማጣራት በተጨማሪ  ሙቅ እና ቀዝቃዛ ውሃ መልቀቅ የሚችሉ  ናቸው፡፡ ማህበሩ ድጋፉን ያደረገው ዳኖን ኑትሪሺያ (DANONE NUTRICIA) ከተባለ የህፃናት ምግብ  አምራች ድርጅት ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ ነው፡፡

 

Tags: 

የኢትዮጵያ ሚድዋይፎች ማህበር የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የሚረዱ የሕክምና መገልገያ ቁሳቁሶችን በሶማሊ ክልል ለሚገኙ አምስት የጤና ተቋማት ድጋፍ አደረገ

የኢትዮጵያ ሚድዋይፎች ማህበር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያስችሉ የሕክምና መገልገያ ቁሳቁሶችን በሶማሊ ክልል ለሚገኙ አምስት የጤና ተቋማት  ድጋፍ አድርጓል፡፡ ማኅበሩ ድጋፉን ያደረገው 28ኛው ዓለም አቀፍ የሚድዋይፎች ቀን ምክንያት በማድረግ መሆኑን የገለጹት የማኅበሩ ክትትል፤ ምዘና እና የምርምር ክፍል ኃላፊው አቶ በለጠ በልጉ ናቸው፡፡ ከድጋፉ መካከል 160 ባለአንድ ሊትር ሳኒታይዘር፣ 295 የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎች፣ 24 ለሕክምና ባለሙያዎች የሚያገለግሉ ሙሉ አልባሳት ይገኙበታል። 

የኢትዮጵያ ሚድዋይፎች ማኅበር 400 ሺህ ብር የሚያወጡ የሕክምና መገልገያ ቁሳቁሶችን በአማራ ክልል ለሚገኙ ስድስት ጤና ተቋማት ድጋፍ አደረገ

የኢትዮጵያ ሚድዋይፎች ማኅበር የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚያግዝ ግምታቸው 400 ሺህ ብር የሆኑ የሕክምና ቁሳቁሶችን ለአማራ ክልል ጤና ቢሮ ድጋፍ አደረገ። ማኅበሩ ድጋፉን ያደረገው 28ኛው ዓለም አቀፍ የሚድዋይፎች ቀን ምክንያት በማድረግ መሆኑን በርክክቡ ወቅት የማኅበሩ ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ መላኩ ታምር ገልጸዋል። ከድጋፉ መካከል 330 ባለአንድ ሊትር ሳኒታይዘር፣ 551 የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎች፣ 53 ለሕክምና ባለሙያዎች የሚያገለግሉ አልባሳት ይገኙበታል። ቁሳቁሶቹ በሽታውን በመከላከል ላይ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ራሳቸውን ከቫይረሱ በመጠበቅ ሙያዊ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያግዛቸው መሆኑን አስረድተዋል።

Tags: 

FOR THE MIDWIVES

Dereje Duguma (MD) (centre), state minister for Health, and Bettina Maas (second from the left), country representative of the United Nations Population Fund, held a press conference on the role of midwives combating the Novel Coronavirus (COVID-19) pandemic on May 7, 2020.

Tags: 

Pages