ማህበሩ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የሚረዱ የሕክምና መገልገያ ቁሳቁሶችን ለደቡብ ክልል ጤና ቢሮ እናቶች እና የህፃናት ጤና አግልግሎቶች ክፍል ድጋፍ አደረገ

የኢትዮጵያ ሚድዋይፎች ማህበር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያስችሉ የሕክምና መገልገያ ቁሳቁሶችን ለደቡብ ክልል ጤና ቢሮ እናቶች እና የህፃናት ጤና አግልግሎቶች ክፍል ድጋፍ አድርጓል ፡፡ ድጋፉ አነስተኛ ቢሆንም በጣም አስፈላጊ እና ሕይወት አድን ስራን ለመስራት የሚያግዝ እንደሆነ ነው የተገለጠው፡፡ በኮቪድ-19 ምክንያት የወሊድ፣ የቤተሰብ እቅድ እና የጨቅላ ሕፃናት ሌሎች የጤና አገልግሎት እንዳይስተጓጎሉ የጋራ ጥረት ማድረግ ይጠበቃል ብለዋል። ቁሳቁሶቹ የተሰጡት በተለይ ሚድዋይፎች በኮቪድ-19 ቫይረስ ለተጠረጠሩ ወይም በቫይረሱ የተያዙ ነፍሰጡር እናቶችን ተገቢውን እንክብካቤ በሚሠጡበት ጊዜ የሚለብሱት ነው:: ማክበር ይህን ድጋፍ ያደረገው በኢትዮጵያ ለ28ኛ ጊዜ የሚከበረውን አለም አቀፍ የሚድዋይፎችን ቀን ታሳቢ በማድረግ መሆኑን የማህበሩ ፕሬዚደንት አቶ ዘነበ አካለ ገልጸዋል::
Tags: