የኮሮና ቫይረስ በሽታ (ኮቪድ-19) ስርጭትን እንዴት መከላከል ይቻላል

የኮሮና ቫይረስ ምንድን ነው?

የኮሮና ቫይረስ እንደ ጉንፋን ከሚመስል ቀላል ህመም አንስቶ እስከ ሳምባ ምች እና የመተንፈሻ ቧንቧ መቆጣት ለመሳሠሉት ከባድ የመተንፈሻ አካላት ህመሞች የሚያጋልጥ የቫይረስ ዝርያ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ የኮሮና ቫይረስ ምንም አይነት የተረጋገጠ ህክምና የለውም።