የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ሊወሠዱ የሚገቡ ጥንቃቄዎች

የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት መንግስት የበሽታውን ስርጭት ለመግታት እና ለመቆጣጠር ተገቢውን እርምጃ እየወሰደ ሲሆን፣ ማህበረሰቡ የሚከተሉት

ን የመከላከያ መንገዶችን ችላ ሳይል እና ሳይደናገጥ ተግባር ላይ በማዋል፣የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የበኩሉን እንዲወጣ ያሳስባል።

  • ሳል ወይም ትኩሳት ካለው ግለሰብ ቢያንስ ሁለት የአዋቂ እርምጃ ርቀት ያህል መራቅ
  • እጅዎን በአግባቡ ሳይታጠቡ አይንና አፍንጫዎን  አይንኩ
  • ከሰዎችጋር አይጨባበጡ፣
  • እጅን በንጹህ ውሃና ሳሙና አዘውትረው ይታጠቡ፣
  • ሰዎች ወደ በሚበዙባቸው ቦታዎች በተለይም የህመም ስሜት ካልዎት አይሂዱ፣
  • በሚያነጥሱበት እና  በሚያስሉበት ጊዜ  አፍና አፍንጫዎን በሶፍት ወይም ክርንዎን  አጥፈው በመጠቀም  ወደ ሌሎች እንዳያስተላልፉ ይጠንቀቁ፣ የተጠቀሙበትን ሶፍትና ተመሳሳይ ነገሮች በቆሻሻ ክዳን ባላቸው ማጠራቀሚያ ያስወግዱ፣
  •  በስራ ቦታ፣በትራንስፖርት እና መኖሪያ ወይም የመኝታ ክፍል መስኮት በመክፈት በቂ   አየር እንዲገባ ማድረግ

http://www.moh.gov.et/ejcc/am/node/194

https://youtu.be/o08p1wBeUPw

 

Tags: