በአገሪቱ ለተመዘገበው የእናቶችና ህፃናት ሞት መቀነስ የሚዲዋይፈሮች ሚና የጎላ ነው፡፡ሚኒስትር ዶ/ር አሚር አማን

በመላው አገሪቱ 55 ሺ ሚዲዋይፈሮች ያስፈልጋሉ ነገር ግን አሁን ላይ 12 ሺ ብቻ ናቸው፡፡ የሚዲዋይፈሮች ማህበር ፕሬዝዳንት የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶ/ር አሚር አማን ለ26 ጊዜ በተከበረው ኛው የአለም አቀፍ የሚዲዋይፈር ቀን ላይ ተገኝተው በአገሪቱ ለተመዘገበው የእናቶችና ህፃናት በጤና መሻሻልና ሞት መቀነስ የሚዲዋፈሮች ሚና የጎላ ነበር ሲሉ ተናግረዋል ፡፡

 

በተለይም በጤናው ዘርፍ ያበረከቱት አስተዋፅኦ ቀላል የሚባል አይደለም ብለዋል፡፡ነገር ግን አሁንም እንክብካቤ የሚሹ እናቶችና ህጻናት እንዳሉም ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡ሚዲዋይፈሮች ከሌሎች ባለሙያዎች በተለየ መንገድ ሁለት ነፍስ የመትረፍ ስራ ነው የሚሰሩት ሲሉ ጠቁመዋል፡፡የሚዲዋይፈሮችን ቁጥርና አቅም ለማሳደግ ሚነስቴር መስርያ ቤቱ ከማህበሩና እና ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር እየሰራን ነው ተናግረው የሚዲዋይፈሪ ባለሙያዎች ሚዲዋይፈር በመሆናቸው ሊኮሩ ይገባል ብለዋል ዶ/ር አሚር አማን፡፡
የሚድዋይፈሪ ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ያለውላይቀር ይልማ በመላው አገሪቱ ማህበሩ ከ5ሺ በላይ አባላት እንዳሉት ጠቁመው የማህበሩ አባላትና ሚዲዋይፈሮችን የጨቅላ ህፃናትና የእናቶች ሞት በመቀነስ ረገድ ድረሻ ነበራቸው ብለዋል፡፡አገሪቱ ከ12 ሺ በላይ የማይበልጡ ሚድዋይፈሮች ያሉ ሲሆን በመላው አገሪቱ ባሉ የጤና ተቋም 55ሺ ሚድዋይፈሮች ያስፈልጋል ብለዋል ፕሬዝዳንቱ፡፡
በ26ኛው አለም አቀፍ የሚዲዋይፈሮች ቀን ሲከበር ጥሩ አፈፃፀም ላሳዩ ጠንካራ ሚዲዋይፈሮች ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡በአሉም በሚዲዋይፈሮች የሚመራ ጥራቱን የጠበቀ እንክብካቤ በሚል መሪ ቃል ተከብሯል፡፡

Tags: