የስድስት ወራት የኮንትራት ቅጥር ማስታወቂያ - ጤና ሚኒስቴር

የስድስት ወራት የኮንትራት ቅጥር ማስታወቂያ

በዓለም ላይ የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በሀገራችን ውስጥም በመከሰቱ መንግስት ወረርሽኙን ለመቆጣጠጠር ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ሲሆን ወደፊት የወረርሽኙ ሁኔታ እየከፋ ከመጣ በርካታ የጤና ባለሙያዎች ማሰማራት አስፈልጓል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች በተጠቀሱት ሙያዎች የተመረቃችሁ እና ከዚህ ቀደም ያልተመዘገባችሁ ሊንኩን በመጫን ከሚያዝያ 7 ቀን 2012 ዓ.ም እስከ ግንቦት 6 ቀን 2012 ዓ.ም ለአንድ ወር ያህል እንድትመዘገቡ እንጠይቃለን፡፡

1. Medicine
2. Public Health Officer
3. Nurse
4. Environmental Health
5. Health Education
6. Pharmacy
7. Medical laboratory
8. Midwife
9. Other Health professionals

Tags: 

መደበኛ የጤና አገልግሎቶች በነበሩበት ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተገለፀ

የኮቪድ-19ን ወረርሽኝን ምክንያት በማድረግ አንድ አንድ የጤና ተቋማት አገልግሎት ማቆማቸው በመደበኛው የጤና አገልግሎቶች ላይ መስተጓጎል እንዳስከተለ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

ለኮሮና ቫይረስ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት ከተለዩት የጤና ተቋማት ዉጪ ሁሉም የጤና ተቋማት እንደተለመደው መደበኛዉን የጤና አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

ዶ/ር ደረጀ አያይዘውም በተለይ በእናቶች እና ህፃናት ጤና አገልግሎት፣ ተላላፊ እና ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ህክምና ላይ መደበኛ አገልግሎት መስጠታቸውን የሚከታተል ግብረ ሀይል ከፌደራል እስከ ወረዳ ድረስ ተቋቁሞ ወደ ስራ ተገብቷል ብለዋል፡፡

Tags: 

Pages